የ3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የ ጥሪ ማስታወቂያ

                                                          ቀን፡ ህዳር 1 2019 ዓ.ም

ለቶርባን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለ አክሲዮኖች የ3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የጥሪ ማስታወቂያ

በኢፌድሪ የንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣367(1)፣370፣371(1)፣ 372 (1) እና 393(2) እንዲሁም በተቋሙ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 18 መሰረት የባለ አክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዕሁድ ታህሳስ 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በሸገር ከተማ በመልካ ኖኖ ክ/ከተማ በሚገኘው ሻቃ ሞል አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡፡

  1. አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
    1.1 የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት የሚገኝበት ቦታ:- አዲስ አበባ ከተማ፤ ልደታ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 10፤የቤት ቁጥር 372
    1.2 የአክሲዮን ማህበሩ የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ቁጥር:- LD/AA/3/0012060/2016
    1.3 የአክሲዮን ማህበሩ የፋይናንስ ስራ ፍቃድ:- MFI/061/2024
    1.4 የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል):- 81,598,000.00 ብር
    1.5 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል):- 45,495,780.00 ብር
  2. የ3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
    2.1 የአክሲዮኖችን ዝውውር እና ባለአክሲዮኖችን ማሳወቅ፡፡
    2.2 እ.ኤ.አ የ2025/2026 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥና መርምሮ ማጽደቅ፡፡
    2.3 እ.ኤ.አ የ2025/2026 የውጪ ኦዲተር ሪፖርት ማድመጥና መርምሮ ማጽደቅ፡፡
    2.4 በ2025/2026 የተገኝውን ትርፍ አደላደልና አወሳሰን የቀረውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ማጽደቅ፡፡
    2.5 የ2026/2027 የውጪ ኦዲተር የስራ ዋጋ መወሰን፡፡
    2.6 የዳይሬክተሮችን የ2025/2026 ጉርሻ ክፍያ መወሰን፡፡
    2.7 የዳሬክተሮችን የ2026/2027 ዓመታዊ የስራ ዋጋ መወሰን፡፡
    2.8 የስራ ዘመናቸውን ባጠናቀቁ የቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማካሄድ፡፡
    2.9 የዕለቱን ቃለ-ጉባዔ አዳምጦ ማጽደቅ፡፡
  3. ማሳሰቢያ
    3.1 ባለአክሲዮኖች በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ቅጂውን ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
    3.2 በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ የማይችሉ ባለአክሲዮኖች እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ወይም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በግንባር ተገኝተው የውክልና ቅጽ ሞልተው ተወካያቸውን መሾም ይችላሉ፡፡

የቶርባን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ