የ2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የ ጥሪ ማስታወቂያ

ለቶርባን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የባለአክሲዮኖች የ2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የ ጥሪ ማስታወቂያ

 

በኢፌድሪ የንግድ አንቀጽ 366(1በኢፌድሪ የንግድ አንቀጽ 366(1) ፣ 367(1) ፣ 370 ፣ 371(1) እና 393(2) እንዲሁም በተቋሙ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 18 መሰረት የባለአክሲዮኖች 2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዕሁድ ታህሳስ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በሸገር ከተማ በመልካ ኖኖ ክ/ከተማ በሚገኘው ሻቃ ሞል አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

  1. አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
    • የአክሺዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት የሚገኝበት ቦታ፦ አዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 101 የቤት ቁጥር 372
    • የአክሲዮን ማህበሩ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ቁጥር፦ LD/AA/3/00120602016
    • የአክሲዮን ማህበሩ የፋይናንስ ስራ ፍቃድ፦ MFI.061/2024
    • የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፦ 81,598,000
    • የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፦ 20,566,000
  2. የ2ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እጀንዳዎች
    • እ.ኤ.አ የ2024/2025 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥና መርምሮ ማጽደቅ፣
    • እ.ኤ.አ የ2024/2025 የውጪ ኦዲተር ሪፖርት ማድመጥና መርምሮ ማጽደቅ፣
    • የ2025/2026 የውጪ ኦዲተር የሥራ ዋጋ መወሰን
    • ያልተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) በአፋጣኝ እንዲከፈል ተወያይቶ መወሰን፣
    • የተጓደለ የቦርድ አባል ማስመረጥ፣
    • የአክሲዮኖችን ዝውውር እና ባለአክሲዮኖችን ማሳወቅ፣
    • የዕለቱን ቃለ-ጉባዔ አዳምጦ ማጽደቅ፣
  3. ማሳሰቢያ
    • ባለአክሺዮኖች በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቅድ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ቅጂውን ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል።
    • በጉባኤው ላይ ለመሳትፍ የማይችሉ ባለአክሲዮኖች እስከ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ወይም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በግንባር ተገኝተው የውክልና ቅጽ ሞልተው ተወካያቸውን ምሾም ይችላሉ።

 

የቶርባን አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ